በሚቀጥሉት አሥራ አንድ ቀናት በአብዛኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፤ ጸሀያማውና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በፀሀይ ኃይል ታግዘው ከሚፈጠሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሸፍን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለይም በደቡብ ምዕራብና በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ማለትም የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል፤ የጉጂና የቦረና ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እየታየ ያለው የበጋው ደረቅና ፀያማ የአየር ሁኔታ ቀጣይነት እንደሚኖረው የሚጠበቅ ሲሆን በአንዳንድ ደጋማ አካባቢዎች ላይ የሌሊቱ እና የማለዳው ቅዝቃዜ በአንፃሩ እንደሚቀንስ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡