Daily Weather Report September 30

Weather Summary for previous day

Sept. 29, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ደቡብ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅ ቦረና፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ዳውሮ፣ ሀዋሳ፣ ጎፋ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በደሎመና 30.9 እና በጊኒር 36.0 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ገዋኔ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ መልካ ጀብዱ፣ ዳሊፋጌ፣ ምዕራብ አባያ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-42.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in Western, South, East, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Jimma, Ilubabor, Kellem, West and East Wollega, East and West Shoa, Bale and East Bale, East Boren, Awi zone, West Gojjam, Agnuak, Majang, Dawuro, Hawasa, Gofa, and South Omo zones. In addition in Delo Mena 30.9 and in Ginir 36.0mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Gambella, Fugnido, Village11, Abobo, Melka Jebdu, Dallifage, Mirab Abaya, Awash Arba, Metehara, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar 35.0-42.4°C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Oct. 1, 2026

በነገው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፣፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow will be cloudy over the western, South East, South, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Kellem, West Wollega, West Arsi, Bale, Guji and West Guji zones of the Oromia region; West, and Centeral Gondar,Awi zone and West Gojam zones of Amhara region; Agnuak, Itang, and Majang zones of Gambella; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Fafan zone of Somali region; All zones of the Sidama region; Yem special Woreda, Halaba, Hadiya, Kambata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Walayita, Gamo, Gofa, and Gedeo zones of South Ethiopia region: Sheka, Keffa, Bench Sheko, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.