Daily Weather Report September 29
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ደቡብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ቦረና፤ አዲስ አበባ፤ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አኝዋክ፣ ቤንች ሸኮ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዳውሮ፣ ሀዋሳ፣ ጋሞ እና ስለጤ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ በመልካ ጀብዱ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ በድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.6-42.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in Western, South, East, South East, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, West and East Wollega, East Shoa, Arsi and West Arsi,Borena; Addis Ababa; North, South, and Centeral Gondar, Awi zone, West and East Gojjam, Agnuak, Bench Sheko, Fafan, Jarar, South Omo, Dawuro, Hawasa, Gamo, and Silte zones. On the other hand, in Semera, Gewane, Gambella, Fugnido, Village11, Abobo, Melka Jebdu, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar 35.6-42.0°C the day time maximum temperatures recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ መካከለኛዉ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፣፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈንና ጃራር ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow will be cloudy over the western, Centeral, East, South East, South, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Kellem, West and East Wollega, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Bale, Guji and West Guji zones of the Oromia region; Harari; West, North and Centeral Gondar,Awi zone and West Gojam zones of Amhara region; Agnuak, Itang, Nuwer, and Majang zones of Gambella; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Fafan and Jarar zones of Somali region; All zones of the Sidama region; Yem special Woreda, Halaba, Hadiya, Kambata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Walayita, Gamo, Basketo, Burji, Konso, Gofa, and Gedeo zones of South Ethiopia region: Sheka, Keffa, Bench Sheko, West Omo, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.