Daily Weather Report September 28

Weather Summary for previous day

Sept. 27, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ደቡብ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ቦረና፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ፤ አዲስ አበባ፤ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ፣ መተከል፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ዳውሮ፣ ሀዋሳ፣ ወላይታ እና ስለጤ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በዳንግላ 30.5 እና በአርጆ 30.4 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ በመልካ ጀብዱ፣ መተሐራ፣ በድሬዳዋ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in Western, South, East, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, West and East Wollega, East, West and South West Shoa, Arsi and West Arsi, Bale, Borena, West and East Hararge; Addis Ababa; North, South, and Centeral Gondar, Awi zone, West and East Gojjam, North and South Wallo, and North Shoa, Metekel, Agnuak, Majang, Dawuro, Hawasa, Walayita, and Silte zones. In addition in Dangila 30.5, and in Arjo 30.4 mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Fugnido, Gambella, Village11, Melka Jebdu, Metehara, Dire Dawa, and Gode 35.0-38.2°C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Sept. 29, 2026

በነገው ዕለት በምዕራብ፣ መካከለኛዉ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ቦረና ና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የአዊ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ዶሎና ጃራር ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow will be cloudy over the western, Centeral, East, South East, South, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Kellem, West Wollega, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Borena and East Borena, Bale, Guji and West Guji zones of the Oromia region; Awi zone of Amhara region; Agnuak, Itang, Nuwer, and Majang zones of Gambella; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; All zones of the Sidama region; Yem special Woreda, Halaba, Hadiya, Kambata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Walayita, Gamo, Basketo, Burji, South Omo, Konso, Gofa, and Gedeo zones of South Ethiopia region: Sheka, Keffa, Bench Sheko, West Omo, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.