Daily Weather Report September 25

Weather Summary for previous day

Sept. 24, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና፣ ደቡብ፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምዕራብ ጎጃም፣ ምስራቅ ትግራይ፤ ጃራር፣ አሶሳ፣ መተከል፣ አኝዋክ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ቡርጂ፣ ጋሞ እና ጌዴኦ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በተልተሌ 31.1፣ በማንኩሽ 48.4፣ በሸርኮሌ 42.4፣ በቻግኒ 33.1 ፣ በባምባሲ 39.5፣ በአምባ16 35.7 እና በማጂ 35.5 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መተሐራ፣ በድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.0-41.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in Western, South, South East, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, West and East Wollega, Bale and East Bale ,Borena , South, West and Centeral Gondar, West and East Gojjam, East Tigray, Jarar, Asosa, Metekel, Agnuak, Dawuro, West Omo, South Omo, Burji, Gamo, and Gedeo zones. In addition in Teltele 31.1, in Mankush 48.4, in Sherkole 42.4, in Chagni 33.1, in Bambase 39.5, in Amba16 35.7, and in Maji 35.5 mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Dallifage, Awash Arba, Fugnido, Melka Jebdu, Metehara, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar 36.0-41.8°C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Sept. 26, 2026

በነገው ዕለት በምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን፣ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንችሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቄለም ወለጋ፣ ማኦኮሞ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow will be cloudy over the western, East, South and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Kellem, East and West Wollega, West and South West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Hararge zones of the Oromia region; Harari; West, North and Centeral Gondar,Awi zone, East and West Gojam zones of Amhara region; Agnuak, Itang, Nuwer, and Majang zones of Gambella; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Fafan zone of Somali region; All zones of the Sidama region; Gurage, East Gurage, Marko special Woreda, Silte, Yem special Woreda, Halaba, Hadiya, Kambata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Walayita, Gamo, Basketo, Burji, Gofa, and Gedeo zones of South Ethiopia region: Sheka, Keffa, Bench Sheko, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region. In addition Kellem, Mao Komo, and West Arsi zone in 24 hours will receive heavy rainfall greater than 30mm. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.