Daily Weather Report September 24
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ፣ ምስራቅና ማዕከላዊ ትግራይ፤ ቆራሄ፣ አሶሳ፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ሸካ፣ ቤንችሸኮ፣ ዳውሮ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ወላይታ እና ጌዴኦ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጊኒር 50.5፣ በፉኝዶ 52.1፣ በቲንሹ ሜጢ 34.6 እና በእርሚቸ 48.8 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ማይሀንሳ፣ በአሸሬ፣ ዳሊፋጌ፣ መተማ፣ በድሬዳዋ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-40.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in Western, North, North East, South, South East, East, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Jimma, Ilubabor, West and East Wollega, Bale and East Bale, West Hararge, Borena and East Borena, Guji and West Guji, Centeral Gondar, South Wallo, West Gojjam, South, East and Centeral Tigray, Korahe, Asosa, Agnuak, Majang, Sheka, Bench Sheko, Dawuro, South Omo, Gamo, Walayita, and Gedeo zones light to moderate rainfall recorded. In addition I Ginir 50.5, in Fugnedo 52.1, in Tinishu Metti 34.6 and in Ermich 48.8 mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Fugnido, Melka Jebdu, Mehoni, Mayhansa, Ashere, Dallifage, Metema, Dire Dawa, and Kebri Dehar 35.0-40.8°C the day time maximum temperatures recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ባሌ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን፣ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንችሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ አርሲ ዞን በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow will be cloudy over the western, East, South and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Kellem, East and West Wollega, West and South West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Hararge zones of the Oromia region; West, North and Centeral Gondar zone of Amhara region; Agnuak, Itang, Nuwer, and Majang zones of Gambella; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Fafan zone of Somali region; All zones of the Sidama region; Marko special Woreda, Silte, Yem special Woreda, Halaba, Hadiya, Kambata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Walayita, Gamo, Basketo, Gofa, and Gedeo zones of South Ethiopia region: Sheka, Keffa, Bench Sheko, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region. In addition West Arsi zone in 24 hours will receive heavy rainfall greater than 30mm. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Gambella, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.