Daily Weather Report September 23
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ድሬዳዋ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ መተከል፣ አኝዋክ፣ ሸካ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ እና ጌዴኦ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአትናጎ 60.0 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ፉኝዶ፣ አዋሽ አርባ፣ በድሬዳዋ፣ በአሸሬ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ማይሀንሳ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.2-41.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in Western, South, South East, East, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Ilubabor, Kellem, West Wollega, Bale and East Bale, West Arsi, West Hararge, Borena and East Borena, Guji and West Guji, West Gojjam, Metekel, Agnuak, Sheka, South Omo, Walayita, and Gedeo zones light to moderate rainfall recorded. In addition Atinago 60.0 mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Fugnido, Awash Arba, Dire Dawa, Ashere, Melka Jebdu, Mehoni, Mayhansa, and Gode 35.2-41.4°C the day time maximum temperatures recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን፣ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንችሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow will be cloudy over the western, East, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Kellem, West Wollega, West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Bale, and East Hararge zones of the Oromia region;West and Centeral Gondar zone of Amhara region; Agnuak, Itang, Nuwer, and Majang zones of Gambella; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Fafan zone of Somali region; All zones of the Sidama region; Marko special Woreda, Silte, Yem special Woreda, Halaba, Hadiya, Kambata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Walayita, Gamo, Basketo, Gofa, and Gedeo zones of South Ethiopia region: Sheka, Keffa, Bench Sheko, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Gambella, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.