Daily Weather Report September 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅና ደቡብ ትግራይ፣ ጋቢ፣ ቆራሄ፣ መተከል፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ዳውሮ፣ ሀዋሳ፣ ወላይታ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ እና ኮንሶ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በሻምቡ 33.5፣ በደምቢ ደሎ 35.3፣ በፉኝዶ 36.0፣ በቦሬ 40.2፣በመንደር11 35.0 እና በቲንሹ ሜጢ32.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አዋሽ አርባ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ማይሀንሳ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-40.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in Western, North, North West, North East, South, South East, East, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Ilubabor, Kellem, Horo Guduru, West Wollega, East and West Shoa, Bale and East Bale, West Arsi, West Hararge, Borena and East Borena, Guji and West Guji; North, South and Central Gondar, Waghemra, North and South Wallo, West and East Gojjam,; North West, Centeral, East, and South Tigray, Gabi, Korahe, Metekel, Agnuak, Majang, Dawuro, Hawasa, Walayita, Gedeo, Gofa, and Konso zones light to moderate rainfall recorded. In addition in Shambu 33.5, in Dambi Dolo 35.3, in Fugnedo 36.0, in Bore 40.2, in Village11 35.0 and in Tinishu Metti 32.2 mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Fugnido, Village11, Awash Arba, Melka Jebdu, Mehoni, Mayhansa, Gode, and Kebri Dehar 35.0-40.8°C the day time maximum temperatures recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለምና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የአዊ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን፣ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንችሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow will be cloudy over the western, East, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Kellem, West Wollega, West Arsi, Guji and West Guji, Bale, East Hararge zones of the Oromia region; Harari; Awi zone of Amhara region; Agnuak, Itang, Nuwer, and Majang zones of Gambella; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Fafan zone of Somali region; All zones of the Sidama region; Marko special Woreda, Silte, Yem special Woreda, Halaba, Hadiya, Kambata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Walayita, Gamo, Basketo, Gofa, and Gedeo zones of South Ethiopia region: Sheka, Keffa, Bench Sheko, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Gambella, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.