Daily Weather Report September 21

Weather Summary for previous day

Sept. 20, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ምዕራብ ና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ፣ አውሲ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ አኝዋክ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ሀዋሳ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጉጉፍቱ 48.6 እና በሜረሳ 35.4 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ዳሊፋጌ፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ መንደር11፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አዋሽ አርባ፣ ምዕራብ አባያ፣ አርባ ምንጭ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-41.6°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in Western, North West, North East, South, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Kellem, East and West Wollega, East Shoa, Bale and East Bale; North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, North and South Wallo, West and East Gojjam, North Shoa, North West and South East Tigray, Awusi, Asosa, Metekel, Agnuak, Bench Sheko, Dawuro, Hawasa, Gamo, Gofa, Gurage and Silte zones light to moderate rainfall recorded. In addition in Guguftu 48.6, and in Mersa 35.4 mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Dallifage, Fugnido, Gambella, Village11, Dire Dawa, Metahara, Awash Arba, Mirab Abaya, Arba Minch, Gode, and Kebri Dehar 35.0-41.6°C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Sept. 22, 2026

በነገው ዕለት በምዕራብ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞንና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፣ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን፣ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንችሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሸካ እና ኢሉባቦር ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow will be cloudy over the western, East, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Kellem, East and West Wollega, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale, West and East Hararge zones of the Oromia region; Dire Dawa; Harari West, North, and Central Gondar, Awi zone, and West Gojjam zones of Amhara region; Agnuak, Itang, Nuwer, and Majang zones of Gambella; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Fafan zone of Somali region; All zones of the Sidama region; Gurage, East Gurage, Marko special Woreda, Silte, Yem special Woreda, Halaba, Hadiya, Kambata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Walayita, Gamo, Basketo, Gofa, and Gedeo zones of South Ethiopia region: Sheka, Keffa, Bench Sheko, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region. In addition Sheka, and Ilubabor zones will receive greater than 30mm in 24 hours. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Gambella, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.