Daily Weather Report September 19

Weather Summary for previous day

Sept. 18, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌ፣ አዲስ አበባ፤ ፤ ድሬዳዋ፤ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሀዋሳ፣ አኝዋክ፣ አሶሳ እና በሸካ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በመተማ 47.2 እና በሞጣ 45.6 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ 36.0፣ በመተማ 35.0 እና በጎዴ 38.0 በ°C የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in Western, North, North East, East, South, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, East Wollega, West Arsi, East Shoa, Bale; Addis Ababa; Dire Dawa: West, South and Central Gondar, Awi zone, North and South Wallo, East Gojjam, Hawasa, Agnuak, Asosa, and Sheka zones light to moderate rainfall recorded. In Metema 47.2, and in Motta 45.6 mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Fugnido 36.0, in Metema 35.0, and in Gode 38.0 in°C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Sept. 20, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን፣ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ቤንችሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue in similar way over the western, northwestern, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, Bale, West and East Hararge, Guji, Borena and East Borena zones of the Oromia region; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, North and South Wallo, West and East Gojjam zones of Amhara region; West, Northwest, and Central zones in Tigray region; Agnuak, and Majang zones of Gambella; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Fafan zone of Somali region; All zones of the Sidama region; Gurage, East Gurage, Marko special Woreda, Silte, Yem special Woreda, Halaba, Hadiya, Kambata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Walayita and Gedeo zones of South Ethiopia region: Sheka, Keffa, Bench Sheko, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Gambella, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Metehara, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.