Daily Weather Report September 14

Weather Summary for previous day

Sept. 13, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ ጉጂ፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ደቡብ ወሎ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ መተከል፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ሀዋሳ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ትግራይ፣ ፋፈን፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጊምቢ 31.5 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ በአቦምሳ፣ አይሻ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in Western, North, North East, East, South, South East, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Jimma, Ilubabor, West Wollega, North, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, East Bale, West and East Hararge, West Guji; Addis Ababa; Harar; South Wallo, East Gojjam, Metekel, Walayita, Gamo, Gofa, Gedeo, south Omo, Hawasa, North West and Centeral Tigray, Fafan, Gurage, and Silte zones light to moderate rainfall recorded. In Gimbi 31.5 mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Fugnido, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Abomsa, Ayisha, Gode, and Kebri Dehar 35.0-38.4 °C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Sept. 15, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ እና ምስራቅ ጉራጌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ቤንችሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ቡኖ በደሌ እና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue in similar way over the northern, western, northwestern, north East, East, south western and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, Bale and East Bale, West and East Hararge, Guji and West Guji, Borena and East Borena zones of the Oromia region; Addis Ababa: Dire Dawa: Harar: West, North, South and Central Gondar, Awi zone, South Wallo, West and East Gojjam, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, and Central zones in Tigray region; Agnuak, Itang, Nuwer, and Majang zones of Gambella; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Sitti and Fafan zones of Somali region; All zones of the Sidama region; Gurage, and East Gurage zones in the Central Ethiopia region; Walayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Kore, Gardula, Burji, south Omo, and Konso zones of South Ethiopia region: Sheka, Keffa, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo zones in the Southwest Ethiopia region; In addition Jimmaa, Buno Bedelle, and West Gojjam zones will receive On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Gambella, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Metehara, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.