Daily Weather Report September 10

Weather Summary for previous day

Sept. 9, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ አዲስ አበባ፤ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ዳውሮ፣ ሀዋሳ፣ ደቡብና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ፣ አውሲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በዳንግላ 47.5፣ በአርጆ 36.4፣ በጊምቢ 36.9፣ በነቀምቴ 45.6፣ በሻምቡ 44.3፣ በካቺሴ 39.0፣ አዲስ አበባ 35.3፣ በማሻ 60.0፣ በጅማ 38.0፣ በቴፒ 53.8፣ በጄምቤ 39.2 እና በቢላምቢሎ 57.0 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መንደር11፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-42.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in Western, Northwest, North, North East, South, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi, Bale; Addis Ababa: North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, North and South Wallo, West and East Gojjam, North Shoa, Asosa, Metekel, Agnuak, Majang, Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Dawuro, Hawasa, Centeral Tigray, Awusi, Gabi, Hari, Gamo, Gedeo, Gurage, and Silte zones light to moderate rainfall recorded. In Dangila 47.5 mm, in Arjo 36.4mm, in Gimbi 36.9, in Nekemte 45.6, in Shambu 44.3mm, in Kachise 39.0mm, in Addis Ababa 35.3mm, in Masha 60.0mm, in Jimma 38.0mm, in Tepi 53.8mm, in Jembe 39.2, and in Bilambilo 57.0mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Fugnido, Gambella, Melka Jebdu, Village11, Mehoni, Dire Dawa, Metehara, Dallifage, Awash Arba, and Gode 35.0-42.4 °C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Sept. 11, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ እና ምስራቅ ጉራጌ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue in similar way over the northern, western, northwestern, north East, East, south western and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Bale, Arsi and West Arsi, West and East Hararge zones of the Oromia region; Addis Ababa: Dire Dawa: Harar: West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, North and South Wallo, West and East Gojjam, Oromo Ethnic special zone, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, East, Central and Southeast zones in Tigray region; Agnuak, Itang, Nuwer, and Majang zones of Gambella; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Sitti and Fafan zones of Somali region; All zones of the Sidama region; Gurage, and East Gurage zones in the Central Ethiopia region; Sheka, and Bench Sheko zones in the Southwest Ethiopia region; In addition North West Tigray, Centeral, North, and South Gondar zones will receive On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Gambella, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Metehara, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.