Daily Weather Report September 09
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ ፋፈን፤ አዲስ አበባ፤ ምዕራብ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ዳውሮ፣ ሀዋሳ፣ ማዕከላዊ ትግራይ፣ ጋሞ ፣ጎፋ፣ ስልጤ እና መተከል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በተርጫ 35.3 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.0-42.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in Western, Northwest, North, North East, South, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Bale, Fafan; Addis Ababa: North, and South Gondar, Awi Zone, West and East Gojjam, Waghemra, North Shoa, Dawuro, Hawasa, Centeral Tigray, Gamo, Gofa, Silte and Metekal zones light to moderate rainfall recorded. In Tercha 35.3 mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Gambella, Abobo, Melka Jebdu, Mayhanes Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Metehara, Dallifage, Awash Arba, and Kebri Dehar 36.0-42.0 °C the day time maximum temperatures recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጉጂ፣ ባሌ፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከአፋር ክልል የቅልበቲ ዞን፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue in similar way over the northern, western, northwestern, north East, East, south western and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji, and Bale zones of the Oromia region; Addis Ababa: Dire Dawa: Harar: West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, North and South Wallo, West and East Gojjam, Oromo Ethnic special zone, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, East, Central and Southeast zones in Tigray region; Agnuak, and Majang zones of Gambella; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Sitti and Fafan zones of Somali region; Siti and Fafan zones of Somali region: Kilbiti zone of Afar region: All zones of the Sidama region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Halaba, Hadiya, Kambata and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Sheka, and Kaffa zones in the Southwest Ethiopia region; On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Gambella, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Metehara, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.