Daily Weather Report September 04

Weather Summary for previous day

Sept. 3, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ፋፈን፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ዳውሮ፣ ሰሜን ምዕራብና ደቡብ ትግራይ እና አሶሳ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአለጌ 76.6 ፣ በሻምቡ 34.3፣ በጅማ 33.6 እና በሀሮ ዶዬ 31.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.2-41.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in Western, Northwest, North, Northeast, East, Southern, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Buno Bedelle, Horo Guduru, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, West Arsi, West and East Hararge: Addis Ababa: Harar: West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North and South Wallo, North Shoa, Fafan, Sheka, Bench Sheko, Keffa, Dawuro, East Tigray, Assosa, and zones light to moderate rainfall recorded. In particular, heavy rainfall was recorded in Alge 76.6, in Shambu 34.3, in Jimma 33.6, and in Haro Doye 31.2 mm. On the other hand, in In Semera, Gewane, Fugnido, Gambella, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Metehara, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar 35.2-41.0°C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Sept. 5, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ቡኖ በደሌ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue in similar way over the northern, western, northwestern, North East, South western, North East, East, and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem Wollega, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi zones of the Oromia region; Addis Ababa: West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North and South Wallo, Oromo Ethnic special zone, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones in Tigray region; Agnuak, Itang, Nuwer, and Majang zones of Gambella; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Sitti and Fafan zones of Somali region; All zones of the Sidama region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Halaba, Hadiya, Kambata and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Sheka, and Kaffa zones in the Southwest Ethiopia region; In addition Centeral Gondar, West Gojam, Buno Bedelle, and East Wollega zones heavy rainfall exceeding 30 mm is expected within 24 hours. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Gambella, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.