Daily Weather Report September 03

Weather Summary for previous day

Sept. 2, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ፣ሸካ፣ሀዋሳ፣ አሶሳ እና መተከል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጨፋ 42.1፣ በደምቢ ዶሎ 30.2፣ በጊምቢ 31.5 እና በነቀምቴ 33.3 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ 38.2፣ ድሬዳዋ 36.0፣ መተሐራ 38.2፣ ጎዴ 37.2 እና ቀብሪደሃር 39.0 በ°C የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in Western, Northwest, North, Northeast, East, Southern, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Buno Bedelle, Horo Guduru, East and West Wollega, East, Southwest and West Shoa, West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North and South Wallo, North Shoa, Centeral, and East Tigray, Assosa, and Metekel zones light to moderate rainfall recorded. In particular, heavy rainfall was recorded in Chefa 42.1mm, in Dambi Dolo 30.2mm, in Gimbi 31.5mm, and in Nekemte 33.3mm. On the other hand, in Gambella 38.2, Dire Dawa 36.0, Metehara 38.2, Gode 37.2 and Kebre Dehar 39.0 in °C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Sept. 4, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን፣ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዴኦ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ ማዕከላዊ ጎንደር እና ምስራቅና ወለጋ ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue in similar way over the northern, western, northwestern, North East, South western, North East, East, and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem Wollega, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, and Bale, zones of the Oromia region; Addis Ababa: Dire Dawa; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North and South Wallo, Oromo Ethnic special zone, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones in Tigray region; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Awusi and Fanti zones of Afar region; Fafan zone of Somali region; All zones of the Sidama region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Halaba, Hadiya, Kambata and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Walayita, and Gedeo zones of South Ethiopia region; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; In addition North West Tigray, Centeral Gondar, and East Wollega zones heavy rainfall exceeding 30 mm is expected within 24 hours. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Gambella, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Metehara, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.