Daily Weather Report October 30
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በደቡብ ኦሞ፣ ሸካ፣ ጋርዶላ፣ ከምባታ፣ ሊበን፣ ሸበሌ፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በወገል ጤና 3.0፣ በአለም ከተማ 3.8፣ በእንዋሪ 5.0፣ በደብረ ብርሃን 4.1፣ በጅግጅጋ 4.0 እና በሐሮማያ 3.8 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as West, and south western parts the country there was cloud coverage. Correspondingly, Light to Moderate rainfall recorded in South Omo, Sheka, Gardula, Kambata, Liban, Shabelle, Awi zone, West Gojam, South Gondar, South West and West Oromia zones. On the other hand, the daytime low temperatures in Wegel Tena 3.0, Alem Ketema 3.8, Enewari 5.0, Debre Berhan 4.1, Jijiga 4.0 and Haromaya 3.8 are recorded as below 5°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዲኦ ዞን፤ በሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን በጥቂት የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Gedeo zone of South Ethiopia region: All zones of the Sidama region; Sheka, Keffa, and Bench Sheko zones in the Southwest Ethiopia region; South west, and Western zones of the Oromia region; Asosa, and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Agnuak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella. On the other hand, the northeast and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy weather, with forecast information’s indicating that the daily minimum temperature will be below 5°C in some highland areas of the country.