Daily Weather Report October 28

Weather Summary for previous day

Oct. 27, 2026

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጎፋ፣ ወላይታ፣ ጌዲኦ፣ ፋፈን፣ ኖጎብ፣ ኤረር፣ ሸበሌ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ኦሮሚያ፤ ሐረር፤ አኝዋክ፣ መተከል፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር እና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአይከል 38.7 እና በጎሬ 33.6 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ ዳሊፋጌ፣ አይሻ፣ ፉኝዶ፣ መተማ፣ መንደር11፣ ማይሃንሳ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 35.0-38.4 °C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as North, North East, East, Centeral, West, and south western parts the country there was cloud coverage. Correspondingly, Light to Moderate rainfall recorded in Gofa, Walayita, Gedeo, Fafan, Nogob, Erer, Shebele, South, South East, West, Centeral, South West and East Oromia; Harar; Agnuak, West and East Gojam, North shoa, Waghemra, North and South Wallo, North, West, Centeral and south Gondar, and Centeral Tigray zones. In Aykel 38.7 and in Gore 33.6 by mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Elidar, Awash Arba, Dallifage, Ayisha, Fugnido, Metema, Village11, Mayhansa, Gode, and Kebri Dehar 35.0- 38.4 the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Oct. 29, 2026

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ቡርጅ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የአዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as East, western, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Gofa, Burji, South Omo, and Gedeo zones of South Ethiopia region: All zones of the Sidama region; Sheka, Keffa, Konta, Bench Sheko, West Omo and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; Dawa, Liban, Afder, Shebele, Korahe, and Doolo zones of Somali region; South, South west, and Western zones of the Oromia region; Asosa, Metekal, Kamashi, and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Agnuak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella; Awi, and West Gojam zones of Amhara region. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Gambella, Fugnido, Village11, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Metahara, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar.