Daily Weather Report October 27
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጎፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጌዲኦ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ኦሮሚያ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ አውሲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በወላይታ 32.5፣ በደምቢ ዶሎ 32.0፣ በጪራ 46.0፣ በጅማ 57.0፣ በደብረ ሲና 55.7፣ በጄምቤ 36.2፣ በቅዳሜ ገበያ 32.7፣ በነቀምቴ 39.3 እና በዳሊፋጌ 48.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ ዳሊፋጌ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ መልካ ጀብዱ፣ ማይሃንሳ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 35.0-39.6 °C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as North, North East, East, Centeral, West, and south western parts the country there was cloud coverage. Correspondingly, Light to Moderate rainfall recorded in Gofa, West Omo, Walayita, Gedeo, Sheka, Bench Sheko, South, South East, West, Centeral, South West and East Oromia; Dire Dawa; Harar; Agnuak, Majang, Awusi, Gabi, Hari, West and East Gojam, North shoa, Waghemra, North and South Wallo, North, Centeral and south Gondar, Centeral, south and East Tigray zones. In Walayita 32.5, in Dambi Dolo 32.0, in Cira 46.0, in Jimma 57.0, in Debre Sina 55.7, in Jembe 36.2, in Kedame Gebeya 32.7, in Nekemte 39.3 and in Dallifage 48.2 by mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Elidar, Awash Arba, Dallifage, Fugnido, Metahara, Mayhansa, Melka Jebdu, Gode, and Kebri Dehar 35.0- 39.6 the day time maximum temperatures recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የኖጎብ፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ ጃራር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የአዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as East, western, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Walayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Burji, Konso, South Omo, and Gedeo zones of South Ethiopia region: All zones of the Sidama region; Sheka, Keffa, Konta, Bench Sheko, West Omo and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; Halaba, Hadiya, Kambata, and Tembaro zones of Centeral Ethiopia region; Nogob, Jarar, Afder, Shebele, Korahe, and Doolo zones of Somali region; South, East, South west, and Western zones of the Oromia region; region; Asosa, Metekal, Kamashi, and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Agnuak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella; Awi, and West Gojam zones of Amhara region. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Gambella, Fugnido, Village11, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Metahara, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar.