Daily Weather Report October 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ መካከለኛዉ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጌዲኦ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ሀዋሳ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛዉ ኦሮሚያ ዞኖች፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ደቡብ፣ ሰሜንና ምዕራብ ጎንደር እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በጊዶሌ 74.0 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መተሐራ እና መተማ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.8-38.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over the southern, southeastern, western, central, northwestern, northeastern, and southwestern parts of our country, where Bega is their second rainy season. In connection with this, light to moderate rainfall was recorded in the Wolayita, Gamo, Gofa, South Omo, Konso, Burji, Gedeo, and West Omo zones; Hawassa; the southern, southwestern, and central zones of Oromia; East and West Gojjam; North and South Wollo; South, North, and West Gondar; and North Shewa zones. Additionally, heavy rainfall 74.0 mm was recorded in Gidole. On the other hand, daily maximum temperatures ranging from 35.8 to 38.0 °C were recorded in Gambella, Fugnido, Metehara, and Metema.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የኖጎብ፣ ዳዋ፣ ፋፈን፣ ሊበን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ምዕራብ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ ፣ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ አማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ትግራይ ክልል በምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡
Tomorrow, cloud coverage will be present over the southern, southeastern, western, eastern, central, and southwestern parts of our country, where Bega is their second rainy season. In connection with this, many places across the Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Burji, Konso, South Omo, and Gedeo zones of the South Ethiopia Region; all zones of the Sidama Region; the Sheka, Keffa, Konta, Bench Sheko, West Omo, and Dawuro zones of the Southwest Ethiopia Peoples' Region; the Yem Special Woreda, Halaba, Hadiya, and Kembata Tembaro zones of the Central Ethiopia Region; the Nogob, Dawa, Fafan, Liben, Jarar, Erer, Afder, Shabelle, Korahe, and Doolo zones of the Somali Region; the southern, southwestern, eastern, central, and western zones of the Oromia Region; Addis Ababa; the Assosa, Kamashi, and Mao Komo zones of the Benishangul-Gumuz Region; the North Wollo, South Wollo, and North Shewa zones of the Amhara Region; the Eastern and Southeastern zones of the Tigray Region; and the Agnuak, Itang, and Majang zones of the Gambella Region will receive light to moderate rainfall (1–29 mm). On the other hand, daily maximum temperatures ranging from 35-40 °C will be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Gambella, Fugnido, Mender 11, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Dire Dawa, Gode, and Kebridahar.