Daily Weather Report October 24

Weather Summary for previous day

Oct. 23, 2026

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በሻሁራ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል ፉኝዶ፣ ምራብ አባያ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 35.2-38.5 °C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over the southern, southeastern, and northwestern parts of our country, where Bega is their second rainy season. In connection with this, light rainfall was recorded in Shahura. On the other hand, maximum daily temperatures ranging from 35.2 to 38.5 °C were recorded in Fugnido, Mirab Abaya, Metehara, Dire Dawa, and Gode.

Weather Forecast for next day

Oct. 25, 2026

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የኖጎብ፣ ዳዋ፣ ፈፋን፣ ሊበን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ምስራቅ እና ምዕራብ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, cloud coverage will be present over the southern, southeastern, western, eastern, and southwestern parts of our country, where Bega is their second rainy season. In connection with this, many places across the Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Burji, Konso, South Omo, and Gedeo zones of the South Ethiopia Regional State; all zones of the Sidama Regional State; the Sheka, Keffa, Konta, Bench Sheko, West Omo, and Dawro zones of the Southwest Ethiopia Peoples' Region; the Yem Special Woreda, Halaba, Hadiya, and Kembata Tembaro zones of the Central Ethiopia Regio; the Nogob, Dawa, Fafan, Liben, Jarar, Erer, Afder, Shabelle, Korahe, and Doolo zones of the Somali Regional State; the southern, southwestern, eastern, and western zones of the Oromia Region; the Assosa and Mao Komo zones of the Benishangul-Gumuz Region; and the Anuak, Itang, and Majang zones of the Gambella Regional State will receive light to moderate rainfall (1–29 mm).
On the other hand, daily maximum temperatures ranging from 35 to 40 °C will be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Gambella, Fugnido, Mender 11, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dalifage, Awash Arba, Metehara, Dire Dawa, Gode, and Kebridahar.