Daily Weather Report October 22

Weather Summary for previous day

Oct. 21, 2026

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በሸካ ዞን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ቢላቴ፣ ማይሀንሳ፣ መልካ ጀብዱ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 35.0-41.0 °C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as south western parts the country cloudy, there was cloud coverage. Correspondingly, Light rainfall recorded in Sheka zone. On the other hand, in Semera, Gewane, Elidar, Awash Arba, Gambella, Fugnido, Bilate, Mayhansa, Melka Jebdu, Metahara, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar 35.0- 41.0 the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Oct. 23, 2026

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን እና አፍዴር ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, cloudy conditions are expected to prevail over the southern, southeastern, western, and southwestern parts of the country, areas that are currently in their second rainy season. Accordingly, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in many areas of Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Burji, Konso, South Omo, and Gedeo zones in the South Ethiopia region; across all zones of the Sidama region; in Sheka, Kaffa, Konta, Bench Sheko, West Omo, and Dawuro zones of the Southwest Ethiopia region; Dawa, Liben, and Afder zones of the Somali region; the southern, southwestern, and western zones of Oromia region; Assosa and Mao-Komo zones of the Benishangul-Gumuz region; and Agnuwak, Itang, and Majang zones of the Gambella region. Meanwhile, maximum temperatures of 35°C to 40°C are expected in Semera, Gewane, Elidar, Gambella, Fugnido, Village 11, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar.