Daily Weather Report October 21
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጥቂት የደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በቡልቂ እና ቦሬ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በኤሊዳር፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ፣ ቀብሪዳሃር፣ ጋምቤላ፣ ፉኚዶ፣ መንደር11 እና አሸሬ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 35.2-41.8 °C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud cover was observed over a few southern and southwestern parts of the country. In connection with this, light to moderate rainfall was recorded in Bulki and Bore. On the other hand, high daily maximum temperatures ranging between 35.2-41.8 °C were recorded in Elidar, Semera, Gewane, Dalifage, Awash Arba, Dire Dawa, Gode, Kebridehar, Gambela, Fugnido, Mender 11, and Ashere.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የባሰኬቶ፣ደቡብ ኦሞ፣ጎፋ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ኮንታ፣ ዳውሮ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ሊበን እና አፍዴር ዞኖች ፤ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ባሌ፣ጂማ፣ ኢሉባቦር እና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ ፣ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the southern, southeastern, western, and southwestern regions of our country, which are experiencing the second rainy season of the bega. In connection with this, many areas in the Basketo, South Omo, Gofa, and Gedeo zones of the South Ethiopia Region; all zones of the Sidama Region; the Sheka, Keffa, Konta, Dawro, and Bench Sheko zones of the Southwest Ethiopia Region; the Liben and Afder zones of the Somali Region; the Guji, West Guji, West Arsi, Bale, Jimma, Illubabor, and Kelem Wollega zones of the Oromia Region; the Assosa and Mao Komo zones of the Benishangul-Gumuz Region; and the Anuak, Itang, Nuer, and Majang zones of the Gambela Region will receive light to moderate rainfall (1–29 mm). On the other hand, daily maximum temperatures ranging between 35 and 40 °C will be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Gambela, Fugnido, Mender 11, Abobo, Melka Jebdu, Ayesha, Dalifage, Awash Arba, Metehara, Dire Dawa, Gode, and Kebridehar.