Daily Weather Report October 20

Weather Summary for previous day

Oct. 19, 2026

በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቡርጅ፣ ጂንካ፣ ጊዶሌ፣ አርባ ምንጭ፣ ቡሌ ሆራ፣ ቦሬ፣ ዲመካ እና ባምባሴ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጊ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ መንደር11፣ ማይሀንሳ፣ መልካ ጀብዱ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 35.4-41.4 °C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud cover was observed over the southern, southwestern, and western parts of our country. In connection with this, light to moderate rainfall was recorded in Burji, Jinka, Gidole, Arba Minch, Bule Hora, Bore, Dimeka, and Bambasi. On the other hand, high daily maximum temperatures ranging between 35.4-41.4 °C were recorded in Semera, Elidar, Gewane, Dalifage, Awash Arba, Dire Dawa, Mender 11, Mayhansa, Melka Jebdu, and Gode

Weather Forecast for next day

Oct. 21, 2026

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የባሰኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ቆራሄ፣ ሸበሌ፣ ሊበን እና አፍዴር ዞኖች ፤ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ኢሉባቦር እና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ ፣ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, cloud cover will prevail over the southern, southeastern, western, and southwestern parts of our country, where Bega their second rainy season. In connection with this, many areas in the Basketo and Gedeo zones of the South Ethiopia Region; all zones of the Sidama Region; the Sheka, Keffa, and Bench Sheko zones of the Southwest Ethiopia Region; the Korahe, Shabelle, Liben, and Afder zones of the Somali Region; the Guji, West Guji, West Arsi, Illubabor, and Kelem Wollega zones of the Oromia Region; the Assosa and Mao Komo zones of the Benishangul-Gumuz Region; and the Anuak, Itang, Nuer, and Majang zones of the Gambela Region will receive light to moderate rainfall (1–29 mm). On the other hand, daily maximum temperatures ranging between 35-40 °C will be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Gambela, Fugnido, Mender 11, Abobo, Melka Jebdu, Ayesha, Dalifage, Awash Arba, Metehara, Dire Dawa, Gode, and Kebridehar.