Daily Weather Report October 17

Weather Summary for previous day

Oct. 16, 2026

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጋሞ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ሀዋሳ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ አኝዋክ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በአርባ ምንጭ 73.2 እና በጎሬ 30.0 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በዳሊፋጌ 36.0 እና በመተሐራ 35.0 በ°C የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as western, Centeral, and south western parts the country cloudy, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall recorded in Gamo, Gofa, Konso, South Omo, Bench Sheko, Dawuro,West Omo, Hawasa, West Guji, Ilubabor, Kellem, East and west Wellega, Agnuak, North Gondar, West and East Gojam zones. In Arba Minch 73.2, and in Gore 31.0 mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Fugnedo 36.0 and in Metahara 35.0 °C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Oct. 18, 2026

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ጃራር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ፤ከኦሮሚያ ክልል የቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የአዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ ፣ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Walayita, Gofa, and Gedeo zones of South Ethiopia region: All zones of the Sidama region; Sheka, Keffa, Konta, Bench Sheko, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; Dawa, Liban, Jarar, Afder, Shebele, Korahe, and Doolo zones of Somali region; Borena and East Borena, Guji and West Guji, Bale, west Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kellem, and West Wollega zones of the Oromia region; Awi zone, and West Gojam zones of Amhara region; Asosa, Metekal, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Agnuak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Gambella, Fugnido, Village11, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Metahara, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar.