Daily Weather Report October 16

Weather Summary for previous day

Oct. 15, 2026

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ሸካ፣ ሀዋሳ፣ ቆራሄ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ አኝዋክ፣ አሶሳ፣ ደቡብና ምስራቅ ትግራይ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ እና አዊ ዞን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በአዴት 30.0 እና በእርሚቸ 31.5 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ ዳሊፋጌ፣ ገዋኔ፣ መተማ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ማይሀንሳ፣ መልካ ጀብዱ፣ ቀብሪደሃር እና በድሬዳዋ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-40.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as western, Centeral, South West, North East and south western parts the country cloudy, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall recorded in Walayita, Gamo, Gofa, Konso, Sheka, Hawasa, Korahe, Borena and East Borena, Bale, Guji and West Guji, Ilubabor, East and west Wellega, East Shoa, Agnuak, Asosa, South and East Tigray, West Gojam, Centeral and South Gondar and Awi zone zones. In Adet 30.0, and in Ermich 31.5 mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Elidar, Dallifage, Gewane, Metema, Awash Arba, Gambella, Fugnido, Mayhansa, Melka Jebdu, Kebri Dehar, and Dire Dawa 35.0-40.8°C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Oct. 17, 2026

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ስለጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኖጎብ፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ፤ከኦሮሚያ ክልል የቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የአዊ ዞን፣ ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ ፣ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, North West, Eastern, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Walayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Burji, Konso, South Omo and Gedeo zones of South Ethiopia region: All zones of the Sidama region; Sheka, Keffa, Konta, Bench Sheko, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; Fafan, Nogob, Dawa, Liban, Jarar, Erer, Afder, Shebele, Korahe, and Doolo zones of Somali region; Borena and East Borena, Guji and West Guji, Bale and East Bale, Arsi and west Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kellem, East and West Wollega, West Shoa, East and West Hararge zones of the Oromia region; Awi zone, Centeral Gondar, East and West Gojam zone of Amhara region; Asosa, Metekal, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Agnuak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Gambella, Fugnido, Village11, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Metahara, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar.