Daily Weather Report October 14
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ወላይታ፣ ጎፋ፣ ቡርጂ፣ ጌዲኦ፣ ዳውሮ፣ ሀዋሳ፣ ጃራር፣ ጉራጌ፣ ስለጤ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ደቡብና ምስራቅ ትግራይ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር እና አዊ ዞን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በጊምቢ 41.5፣ በጊዳ አያና 38.2 እና በመንደር11 63.5 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ ዳሊፋጌ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ መልካ ጀብዱ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ እና በቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-40.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as western, Centeral, South West, North East and south western parts the country cloudy, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall recorded in Addis Ababa; Walayita, Gofa, South Omo, Burji, Gedeo, Sheka, Dawuro, Hawasa, Jarar, Gurage, Silte, East Borena, Bale and East Bale, West Guji, Ilubabor, Buno Bedele, Kellem, East and west Wellega, East and West Shoa, West Hararge, Agnuak, Majang, Asosa, Metekel, SouthEast and West Gojam, North and Centeral Gondar and Awi zone zones. In Gimbi 41.5, in Gida Ayana 38.2 and in Village11 63.5mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Elidar, Dallifage, Awash Arba, Gambella, Fugnido, Village11, Melka Jebdu, Metahara, Dire Dawa, and Kebri Dehar 35.0-40.4°C the day time maximum temperatures recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኖጎብ፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ፤ከኦሮሚያ ክልል የቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ ፣ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሸካ፣ ጃራር፣ ቆራሄ፣ ኤረር፣ እና በሸበሌ ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, Eastern, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Walayita, Gamo, Gofa, and Gedeo zones of South Ethiopia region: All zones of the Sidama region; Sheka, Keffa, Konta, Bench Sheko, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; Fafan, Nogob, Dawa, Liban, Jarar, Erer, Afder, Shebele, Korahe, and Doolo zones of Somali region; Borena and East Borena, Guji and West Guji, Bale and East Bale, Arsi and west Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kellem, East and West Wollega, East and West Hararge zones of the Oromia region; Awi zone, East and West Gojam zone of Amhara region; Asosa, Metekal, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Agnuak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Gambella, Fugnido, Village11, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Metahara, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar.