Daily Weather Report October 13
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በሐረር፤ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጌዲኦ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ሀዋሳ፣ ጃራር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ጉራጌ፣ ስለጤ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ደቡብ፣ ምስራቅና ማዕከላዊ ትግራይ፣ አውሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ደቡብ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር እና አዊ ዞን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በቡርጂ 32.4፣ በአዴት 60.0፣ በጎዴ 68.0፣ በመረሳ 57.4፣ በአትናጎ 45.0፣ በአሶሳ 35.2፣ በሺላቦ 49.0፣ በአባ ጃራ 39.0 እና በቅዳሜ ገበያ 37.9 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ማይሀንሳ እና በቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-41.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as western, Centeral, South West, North East and south western parts the country cloudy, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall recorded in Harar; Walayita, Gamo, Gofa, South Omo, Konso, Burji, Gedeo, Sheka, West Omo, Hawasa, Jarar, Afder, Shebele, Gurage, Silte, Borena and East Borena, Bale and East Bale, West Guji, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kellem, East and west Wellega, West Shoa, East Hararge, Agnuak, Majang, Asosa, Metekel, SouthEast and West Gojam, North and Centeral Gondar and Awi zone zones. In In Kedame Gebeya 38.6mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Elidar, Dallifage, Gambella, Fugnido, Village11, Melka Jebdu, Aysha, Ashere, Hagre Selam, Metahara, Dire Dawa, Gode, and Kedame Gebeya 35.0-41.8°C the day time maximum temperatures recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኖጎብ፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ፤ከኦሮሚያ ክልል የቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የአዊ ዞን፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ ፣ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጃራር፣ ቆራሄ እና በዶሎ ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, Eastern, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Walayita, Gamo, Gofa, and Gedeo zones of South Ethiopia region: All zones of the Sidama region; Sheka, Keffa, Konta, Bench Sheko, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; Fafan, Nogob, Dawa, Liban, Jarar, Erer, Afder, Shebele, Korahe, and Doolo zones of Somali region; Borena and East Borena, Guji and West Guji, Bale and East Bale, Arsi and west Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kellem, East and West Wollega, East and West Hararge zones of the Oromia region; Awi zone, East and West Gojam zone of Amhara region; Asosa, Metekal, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Agnuak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Gambella, Fugnido, Village11, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Metahara, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar.