Daily Weather Report October 12
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በወላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ጋሞ፣ ጌዲኦ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ አኝዋክ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር እና አዊ ዞን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ ያገኙ ሲሆን፤ በደሎመና 45.5፣ በጋምቤላ 41.2፣ በጊኒር 35.0፣ በጎሮ በከክሳ 35.0፣ በነገሌ 32.5፣ በቡሌ ሆራ 30.1 እና በጊዶሌ 31.8 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ዳሊፋጌ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ አሸሬ፣ ሀገረ ሰላም፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና በቅዳሜ ገበያ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-41.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as western, South West and south western parts the country cloudy, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall recorded in Walayita, South Omo, Konso, Gamo, Gedeo, West Omo, Korahe, Shebele, Borena and East Borena, Bale and East Bale, West Guji, Jimma, Ilubabor, Kellem, East and west Wellega, Agnuak, East and West Gojam, North and Centeral Gondar and Awi zone zones. In In Kedame Gebeya 38.6mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Elidar, Dallifage, Gambella, Fugnido, Village11, Melka Jebdu, Aysha, Ashere, Hagre Selam, Metahara, Dire Dawa, Gode, and Kedame Gebeya 35.0-41.8°C the day time maximum temperatures recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ፤ከኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ ፣ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, Eastern, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Walayita, Gamo, Gofa, and Gedeo zones of South Ethiopia region: All zones of the Sidama region; Sheka, Keffa, Konta, Bench Sheko, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; Fafan, Nogob, Jarar, Erer, Afder, Shebele, Korahe, and Doolo zones of Somali region; East Borena, Guji and West Guji, Bale, Arsi and west Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kellem, East and West Wollega, West and South West Shoa, East and West Hararge zones of the Oromia region; Harari; Centeral and South Gondar, Awi zone, North and South Wallo, East and West Gojam zone of Amhara region; Asosa, Metekal, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Agnuak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Gambella, Fugnido, Village11, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Metahara, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar.