Daily Weather Report October 08

Weather Summary for previous day

Oct. 7, 2026

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ወላይታ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ሸካ፣ ቆራሄ፣ ኤረር፣ በቦረና፣ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ኢሉባቦር፣ አዊ ዞን እና ቄለም ወለጋ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቀብሪደሃር 32.4 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጌ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መልካ ጀብዱ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.0-42.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as western, and south western parts the country cloudy, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall recorded in Walayita, Gofa, South Omo, West Omo, Sheka, Korahe, Erer, Borena, Guji, Bale and East Bale, Ilubabor, Awi zone Kellem Wollega, Zones. In Kebri Dehar32.4 heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Dallifage, Elidar, Awash Arba, Gambella, Fugnido, Melka Jebdu, Metahara, Dire Dawa, and Gode 36.0-42.0°C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Oct. 9, 2026

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የባሰኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኖጎብ፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ፤ከኦሮሚያ ክልል የቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ ማንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Basketo, and Gedeo zones of South Ethiopia region: All zones of the Sidama region; Sheka, Keffa, Konta, Bench Sheko, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; Fafan, Nogob, Dawa, Liban, Jarar, Erer, Afder, Shebele, Korahe, and Doolo zones of Somali region; Borena and East Borena, Guji and West Guji, Bale and East Bale, Jimma, Ilubabor, Kellem Wollega zones of the Oromia region; Asosa, and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Agnuak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Village11, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar.