Daily Weather Report October 06
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዲኦ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብኦሞ፣ ዳውሮ፣ ሀዋሳ፣ ሸበሌ፣ በቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅ ጎጃም፣ አሶሳ፣ አኝዋክ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጊኒር 54.0፣ መንደር11 119.0፣ በእርሚቸ 34.1፣ ድሬሼክ ሁሴን 85.5 እና በጎንደር 30.0 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ አይሻ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር11፣ አሸሬ፣ መልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-43.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as western, North East and south western parts the country cloudy, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall recorded in Walayita, Gamo, Gofa, Konso, South Omo, Gedeo, Sheka, Keffa, Bench Sheko, West Omo, Dawuro, Hawas, Shebele, Borena and East Boren, Bale and East Bale, Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East and West Wollega, North and Centeral Gondar, Awi zone, West Gojam, Asosa, Agnuak, and East Tigray zones. In Ginir 54.0, in Village11 119.0, in Ermich 34.1, in DireShek Husen 85.5 fi in Gondar 30.0 heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Elidar, Awash Arba, Ayisha, Gambella, Fugnido, Village11, Ashere, Melka Jebdu, Dire Dawa, and Gode 35.0-43.8°C the day time maximum temperatures recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኖጎብ፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ፤ከኦሮሚያ ክልል የቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ማንደር11፣ አቦቦ፣ መልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, East, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Walayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Burji, Konso, South Omo and Gedeo zones of South Ethiopia region: All zones of the Sidama region; Sheka, Keffa, Konta, Bench Sheko, West Omo and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; Yem special woreda, Halaba, Hadiya, Kambata and Tembaro; Fafan, Nogob, Dawa, Liban, Jarar, Erer, Afder, Shebele, Korahe, and Doolo zones of Somali region; Borena and East Borena, Guji and West Guji, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kellem, East and West Wollega, West and East Hararge zones of the Oromia region; Harari; North, South and Centeral Gondar, Awi zone, and East Gojam zones of Amhara region; Asosa, Metekal, Kamashi, and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Agnuak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Gambella, Fugnido, Village11, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Dire Dawa, Gode, and Kebri Dehar.