Daily Weather Report October 02
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በምስራቅ ወለጋ፣ ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ማዕከላዊ ጎንደር፣ አኝዋክ፣ ቤንች ሸኮ፣ አሶሳ፣ ሸበሌ፣ ቡርጂ፣ ጎፋ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በእርሚቸ 39.2ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ገዋኔ፣ ፉኝዶ፣ አዋሽ አርባ፣ አይሻ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36-42.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in Western, South, South East, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in East Wollega, Bale and East Bale, Borena and East Boren, Centeral Gondar, Agnuak, Bench Sheko, Asosa, Shebele, Burji, Gofa, and South Omo zones. In addition in Ermich 39.2 mm heavy rainfall recorded. On the other hand, in Semera, Gewane, Fugnido, Awash Arba, Ayisha, Metehara, Dire Dawa, Kebri Dehar and Gode 35.5-43.0°C the day time maximum temperatures recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና
ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ሐረሪ፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኖጎብ፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow will be cloudy over the western, South East, South, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Kellem Wollega, West Arsi, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Guji and West Guji zones of the Oromia region; Agnuak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella; Asosa, and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Fafan, Nogob, Dawa, Liban, Jarar, Erer, Afder, Shebele, Korahe, and Doolo zones of Somali region; All zones of the Sidama region; Walayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Burji, Konso, South Omo and Gedeo zones of South Ethiopia region: Sheka, Keffa, Bench Sheko, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Aysha, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.