Daily Weather Report November 27
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች፣ በምስራቅ እና በሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና መካከለኛው ኦሮሚያ፣ በጋሞ፣ በምዕራብ ኦሞ፣ ሀዲያ፣ ሀዋሳ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ በሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ደቡባዊ ትግራይ ዞኖች በጥቂት ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ ጋምቤላ፣ መተሃራ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪ ደሃር እና በጎዴ ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት መጠን ከ35.0°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Southwestern, southern, central, southern high lands, eastern and northern parts of the country had better cloud coverage during the previous day. In line with this, light to moderate rainfall was recorded at few places of Southwest, South, West and Central Oromia, Gamo, West Omo, Hadiya, Hawassa, East Gojjam, North and South Wollo, North Shoa, and South Tigray zones. On the other hand, the daytime maximum temperature exceeded 35.0°C at Matema, Elidar, Fugnido, Gambella, Metehara, Awash Arba, Kebri Dehar, and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ ደቡብ ደጋማ ስፍራዎች፣ በመካከለኛዉ፣ ምስራቅ እና ሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፣ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዴኦ እና ባስኬቶ ዞኖች፣ ከጋምቤላ ከልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በቋራ፣ በመተማ፣ በማንኩሽ፣ በላሬ፣ በጎዴ፣ በአቦቦ፣ በጋምቤላ፣ በፉኝዶ እና በአዋሽ አርባ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
The southwestern, southern, southern highland, central, eastern, and northern parts of the country are expected to have better cloud coverage for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall, ranging from 1 to 29 mm, is expected across many areas in Southwest, West, Central, East, South, and Southeast zones of the Oromia region; East Gojjam, North and South Wello, and North Shoa zones of the Amhara region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench-Sheko, Konta, West Omo, and Dawuro zones of the Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; Wolaita, Gamo, Gofa, Gedeo, and Basketo zones of the South Ethiopia region; and Agnuwak, and Majang zones of the Gambella region. On the other hand, daytime maximum temperatures ranging from 35°C to 40°C are expected to be recorded in Quara, Metema, Mankush, Lare, Gode, Abobo, Gambella, Fugnido and Awash Arba.