Daily Weather Report November 26
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው ኦሮሚያ፣ በጎፋ፣ በዳውሮ፣ በዎላይታ፣ ሀዋሳ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ በሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ማዕከላዊ እና ምስራቃዊ ትግራይ ዞኖች በጥቂት ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በጋምቤ እና በጎዴ ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት መጠን ከ35.0°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Southwestern, central, southern high lands and northern parts of the country had better cloud coverage during the previous day. In line with this, light to moderate rainfall was recorded at pocket places of Southwest and Central Oromia, Gofa, Dawro, Wolaita, Hawassa, East Gojjam, north Wollo, north Shoa, central and east Tigray. On the other hand, the daytime maximum temperature exceeded 35.0°C at Fugnido, Gambella, and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ ደጋማ ስፍራዎች፣ በመካከለኛዉ፣ ምስራቅ እና ሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፣ አዲስ አበባ፣ ከአማራ ክልል የደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግህምራ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡባዊ ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፣ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ጋርዱላ፣ ጌዴኦ እና ባስኬቶ ዞኖች፣ ከጋምቤላ ከልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በመካከለኛዉ ኦሮሚያ እና ምስራቅ አማራ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በመንደር 11፣ በተርኮዲ፣ በሸርቆሌ፣ በቋራ፣ በመተማ፣ በማንኩሽ፣ በላሬ፣ በጎዴ፣ በአቦቦ፣ በፉኝዶ፣ በአዋሽ አርባ፣ በኤሊዳር እና በጋምቤላ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
The southwestern, southern, southern highland, southeastern, central, eastern, and northern parts of the country are expected to have better cloud coverage for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall, ranging from 1 to 29 mm, is expected across many areas in Southwest, Central, East, South, and Southeast zones of the Oromia region; Addis Ababa; South Gondar, East Gojjam, Wag-Himra, North and South Wello, Oromo ethnic special zone, and North Shoa zones of the Amhara region; Eastern, Southeastern, and Southern zones of the Tigray region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, West Omo, and Dawro zones of the Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; Wolaita, Gamo, Gofa, Burji, Konso, Gardula, Gedeo, and Basketo zones of the South Ethiopia region; and Agnuwak, and Majang zones of the Gambella region. In addition, unseasonal rainfall is likely to occur over some places of Central Oromia and eastern Amhara regions. On the other hand, daytime maximum temperatures ranging from 35°C to 40°C are expected in Village 11, Terkodi, Sherkole, Quara, Metema, Mankush, Lare, Gode, Abobo, Fugnido, Awash Arba, Elidar, and Gambella.