Daily Weather Report November 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው ኦሮሚያ፣ በቤንች ሸኮ፣ በምዕራብ ኦሞ፣ በሀዲያ፣ በጉራጌ፣ በምስራቅ ጎጃም፣ በሰሜን እና ደቡብ ወሎ እንዲሁም ሰሜን ሸዋ፣ በሀዋሳ እና ምስራቅ ትግራይ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ በጎዴ፣በቀብሪ ደሃር፣ እና በመተማ ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት መጠን ከ35.0°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Southwestern, central, southern high lands and northern parts of the country had better cloud coverage during the previous day. In line with this, light to moderate rainfall was recorded at some places of Southwest and Central Oromia, East Gojjam, north and south Wollo as well as north Shoa, Bench- Sheko, west Omo, Hadiya, Gurage, Hawassa and east Tigray. On the other hand, the daytime maximum temperature exceeded 35.0°C at Fugnido, Gambella, Gode, Kebri-Dehar and Metema.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ ደቡብ ደጋማ ስፍራዎች፣ በመካከለኛዉ፣ ምስራቅ እና ሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፣ አዲስ አበባ፣ ከአማራ ክልል የደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ዋግህምራ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡባዊ ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፣ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዴኦ እና ባስኬቶ ዞኖች፣ ከጋምቤላ ከልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በጎዴ፣ በአቦቦ፣ በፉኝዶ፣ በላሬ፣ በቋራ፣ በሸርቆሌ፣ በተርኮዲ፣ በአዋሽ አርባ፣ በኤሊዳር እና በመተማ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
The southwestern, southern, southern highland, central, eastern, and northern parts of the country are expected to have better cloud coverage for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall, ranging from 1 to 29 mm, is expected in many areas in West, Southwest, Central, East, South, and Southeast zones of the Oromia region; Addis Ababa; South Gondar, East and West Gojjam, Wag-Himra, North and South Wello, Oromo ethnic special zone, and North Shoa zones of the Amhara region; Eastern, Southeastern, and Southern zones of the Tigray region; Gurage, East Gurage, Mareko Special Woreda, Silte, Yem Special Woreda, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, West Omo, and Dawro zones of the Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; Wolaita, Gamo, Gofa, Gedeo, and Basketo zones of the South Ethiopia region; and Agnuwak, Itang, Nuwer, and Majang zones of the Gambella region. In addition, unseasonal rainfall is likely to occur over some places of the country. On the other hand, daytime maximum temperatures ranging from 35°C to 40°C are expected in Gode, Abobo, Fugnido, Lare, Quara, Sherkole, Terkodi, Awash Arba, Elidar, and Metema.