Daily Weather Report November 24
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ, በመካከለኛው እና በሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ ኦሮሚያ፣ በአኙዋክ፣ በምስራቅ ጎጃም፣ በሰሜን ወሎ እና አኙዋክ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በጎዴ፣ በኤሊዳር፣ በአዋሽ አርባ እና በመተማ ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት መጠን ከ35.0°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Southwestern, central and northern parts of the country had cloud coverage during the previous day. In line with this, light rainfall was recorded at few places of Southwest and West Oromia; Agnuwak, East Gojjam and North Wollo zones. On the other hand, the daytime maximum temperature exceeded 35.0°C at Fugnido, Gode, Elidar, Awash Arba and Metema.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ ደቡብ ደጋማ ስፍራዎች፣ በመካከለኛዉ እና ሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል የደቡብ ጎንደር፣ አዊ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የደቡባዊ ዞን፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፣ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዴኦ እና ባስኬቶ ዞኖች፣ ከጋምቤላ ከልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማዣንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጎዴ፣ በፉኝዶ፣ በአዋሽ አርባ፣ በኤሊዳር እና በመተማ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, cloud cover is expected over the southwestern, southern, southern highland, central, and northern parts of the country. In association with this, many areas of the West, Southwest, southeast and Centra zones of Oromia region; the South Gondar, Awi, East and West Gojjam, North Wollo, South Wollo, and North Shewa zones of the Amhara region; the Southern zones of Tigray region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zone of the Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench-Sheko, Konta, West Omo and Dawro zone of Southwest Ethiopia region; all zones of Sidama region; Wolaita, Gamo, Gofa, Gedeo, and Basketo zones of the South Ethiopia region; and the Aguwak, Itang, Nuwer and Majang zones of Gambella will receive light to moderate rainfall (1–29 mm). Meanwhile, daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded at Gode, Fugnido, Awash Arba, Elidar, and Metema.