Daily Weather Report November 23
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ, በመካከለኛው እና በሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብና መካከለኛ ኦሮሚያ፣ በአኙዋክ፣ በአዊ፣ በመዕራበና ምስራቀ ጎጃም እንዲሁም በሰሜን ወሎ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በጎዴ፣ በኤሊዳር፣ በቀብሪደሃር፣ በጋምቤላ፣ በአዋሽ አርባ እና በፓዌ ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት መጠን ከ35.0°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Southwestern, central and northern parts of the country had better cloud coverage during the previous day. In line with this, light to moderate rainfall was recorded at some places of Southwest, West, and Central Oromia; Agnuwak zone of Gambella, West and East Gojjam, as well as North Wollo zones. On the other hand, the daytime maximum temperature exceeded 35.0°C at Fugnido, Gode, Elidar, Kebri Dahar, Gambella, Awash Arba and Pawe.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ ደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና ሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛው ደቡብ ምስራቅ፣ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ እና ባስኬቶ ዞኖች፣ ከጋምቤላ ከልል የአኙዋክ እና ማዣንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጎዴ፣ በፉኝዶ፣ በአዋሽ አርባ፣ በኤሊዳር፣ በጋምቤላ እና በቀብሪደሃር ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Cloud cover is expected over the southwestern, central, southern highland and northern parts of the country. In association with this, many areas of the West, Southwest, southeast and Centra zones of Oromia region; North, South and Central Gondar, Awi, East and West Gojjam, and North and South Wollo zones of the Amhara region; the Southern and Southeastern zones of Tigray region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zone of the Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench-Sheko, Konta and Dawro zone of Southwest Ethiopia region,; all zones of Sidama region; Wolaita, Gofa and Basketo zone of the South Ethiopia region; and the Agnuwak and Majang zones of Gambella region will receive light to moderate rainfall (1–29 mm). Meanwhile, daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected at Gode, Fugnido, Awash Arba, Elidar, Gambella and Kebri Dahar.