Daily Weather Report November 20

Weather Summary for previous day

Nov. 19, 2026

በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ, በመካከለኛው እና በሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ፣ በምስራቅ ጎጃም፣ በማዕከላዊ ጎንደር፣ በሰሜን ወሎ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ምስራቃዊ ትግራይ ማዕከላዊ ዞኖች በጥቂት ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በጎዴ፣ በቀብሪደሃር እና በመተማ ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት መጠን ከ35.0°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Southern, southwestern, central and northern parts of the country had cloud coverage during the previous day. In line with this, light to moderate rainfall was recorded in a few places of southwest, west, south and southeast Oromia, East Gojjam, Central Gondar, North Wollo, and the northwestern, central and eastern zones of Tigray. On the other hand, the daytime maximum temperature exceeded 35.0°C at Fugnido, Gode, Kebri Dahar and Metema.

Weather Forecast for next day

Nov. 21, 2026

በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ ደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና ሰሜን እንዲሁም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት የደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ ምስራቅና ደቡብ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፣ ከጋምቤላ ከልል የአኙዋክ እና ማዣንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጎዴ፣ በመተሃራ፣ በፉኝዶ፣ በቀብሪደሃር እና በመተማ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

The southwestern, central, southern highland, and northern parts as well as the southern parts of Ethiopia, which are currently experiencing their second rainy season during the bega season will have cloud coverage for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall, ranging from 1 to 29 mm, is expected in many areas of the western, southwestern, central, southeastern, and southern zones of the Oromia region; West, North, South, and Central Gondar, Awi, East and West Gojjam, zones of the Amhara region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, and Dawro zones of the Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; Wolaita, Gofa, Basketo, and Gedeo zones of the South Ethiopia region; and the Aguwak and Majang zones of the Gambella region. On the other hand, daytime maximum temperatures ranging from 35°C to 40°C are expected to be recorded in Gode, Metehara, Fugnido, Kebridehar, and Metema.