Daily Weather Report November 19

Weather Summary for previous day

Nov. 18, 2026

በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ, በመካከለኛው፣ ምስራቅ እና በሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና መካከለኛው ኦሮሚያ፣ እንዲሁም ምስራቅ ጎጃም እና የትግራይ ማዕከላዊ ዞኖች በጥቂት ቦታዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በጎዴ፣ በቀብሪደሃር፣ በሰመራ እና አዋሽ አርባ ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት መጠን ከ35.0°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Cloud cover was observed over the southern, southwestern, central, eastern, and northern parts of the country. In line with this, light to moderate rainfall was recorded in a few places of the Southwest, West, and Central Oromia, as well as East Gojam and Central Tigray zones. On the other hand, daytime maximum temperatures exceeded 35.0 °C in Fugnido, Gode, Kebri Dehar, Semera, and Awash Arba.

Weather Forecast for next day

Nov. 20, 2026

በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ ደቡብ ደጋማ ስፍራዎች፣ በምስራቅ እና ሰሜን እንዲሁም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት የደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅና ደቡብ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ አዊ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፣ ከትግራይ ከልል ማዕከላዊ እና ምስራቃዊ ዞኖች፣ እንዲሁም ከሱማሌ ከልል የዳዋ እና ሊበን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጎዴ፣ በመተሃራ፣ በአዋሽ አርባ እና በሰመራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Cloud cover is expected to enhance over the southwestern, central, southern highlands, eastern and northern Ethiopia, as well as the southern and southeastern parts of the country, which are currently experiencing their second rainy season during the Bega period. In association with this, light to moderate rainfall, ranging from 1 to 29 mm, is expected across several areas of the West, Southwest, Central, East, Southeast, and South zones of Oromia region; North, South, and Central Gondar, Wag-Himra, North and South Wollo, Awi, East and West Gojjam, the Oromo ethnic special zone, and North Shoa zones of the Amhara region; Gurage, East Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones, as well as Mareko and Yem special woredas of the Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, and Dawro zones of the Southwest Ethiopia region; all zones of Sidama region; Wolaita, Gofa, Basketo, and Gedeo zones of the South Ethiopia region; the Central and Eastern zones of Tigray region; as well as the Dawa and Liben zones of the Somali region. Meanwhile, daytime maximum temperatures are expected to be recorded in the range between 35°C and 40°C over Fugnido, Gode, Metehara, Awash Arba, and Semera.