Daily Weather Report November 17

Weather Summary for previous day

Nov. 16, 2026

በትናንትናው ዕለት ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ አመዝኖባቸው ተስተዉሏል፡፡ ይሁን እንጂ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በምዕራብ ኦሞ እና ደቡብ ኦሮሚያ ጥቂት ቦታዎች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በአዋሽ አርባ፣ በጎዴ፣ በቀብሪ ደሃር፣ በገዋኔ፣ በሰመራ እና በኤሊዳር ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት መጠን ከ36.0°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Dry, sunny and windy conditions persisted over most parts of the country during the previous day. However, cloud cover was observed over the southern, southwestern and northern parts of the country. In association with this, light rainfall was recorded over pocket places of West Omo and South Oromia. On the other hand, daily maximum temperatures above 36.0 °C were recorded at Gambella, Awash Arba, Gode, Kebri-Dahar, Gewane, Semera and Elidar.

Weather Forecast for next day

Nov. 18, 2026

በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ ደቡብ ደጋማ ስፍራዎች፣ ምስራቅ እና ሰሜን እንዲሁም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት የደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅና ደቡብ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ኮሬ እና ጌዴኦ ዞኖች፣ ከትግራይ ከልል ማዕከላዊ እና ምስራቃዊ ዞኖች፣ እንዲሁም ከሱማሌ ከልል የዳዋ እና ሊበን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በተርኮዲ፣ መንደር11፣ በቋራ፣ በላሬ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በማንኩሽ፣ በሸርቆሌ፣ በኢታንግ እና በመተማ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, cloud cover is expected over the southwestern, central, southern highland, eastern and northern parts of the country, as well as the southern and southeastern Ethiopia that are currently experiencing their second rainy season. In association with these, light to moderate rainfall (1–29 mm) is likely to occur in several areas of West, Southwest, Central, East, Southeast and South zones of Oromia region; North, South and Central Gondar, Wag Himra, North and South Wollo, the Oromo Ethnic special zone, East Gojjam and North Shoa in Amhara region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones in Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, West Omo and Dawuro in Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Ari, Konso, Gardula, Burji, Korie, Ale and Gedeo zones in South Ethiopia region; Eastern and Central zones in Tigray region; and Dawa and Liben zones of Somali Region. Meanwhile, daily maximum temperatures of 35 to 40 °C are expected at Terkodi, Mender11, Quara, Lare, Fugnido, Abobo, Mankush and Metema.