Daily Weather Report November 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ አመዝኖባቸው ተስተዉሏል፡፡ ይሁን እንጂ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በምዕራብ ጎጃም እና ምዕራብ ኦሮሚያ ጥቂት ቦታዎች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ በአዋሽ አርባ፣ በጎዴ እና በቀብሪ ደሃር ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.0°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Dry, sunny and windy conditions prevailed over most parts of the country during the previous day. However, the southern, southwestern and western areas had cloud coverage. In line with this, light rainfall was recorded at a few places in West Gojjam and West Oromia. Meanwhile, maximum temperatures exceeded 36.0°C at Metema, Awash Arba, Gode and Kebri Dahar.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛዉ፣ ደቡብ ደጋማ ስፍራዎች፣ ምስራቅ እና ሰሜን እንዲሁም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅና ደቡብ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ እና ጌዴኦ ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የዳዋ እና ሊበን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ጥቂት ቦታዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በተርኮዲ፣ መንደር11፣ በቋራ፣ በላሬ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በማንኩሽ እና በመተማ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, cloud cover is expected across southwestern, central, eastern, northern and southern highland areas of the country, as well as parts of southern Ethiopia that are currently experiencing their second rainy season. In association with these, light to moderate rainfall (1–29 mm) is likely to occur in several areas of the southwestern, central, eastern, southeastern and southern zones of Oromia region; North, South and Central Gondar, Wag-Himra, North and South Wollo, and East Gojjam in Amhara region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro in Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench- Sheko, Konta, West Omo and Dawuro zones in Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones in South Ethiopia region; and Dawa and Liben zones of Somali Region. In addition, a few areas of southwestern Oromia are likely to experience heavy rainfall, with amounts exceeding 30 mm within 24 hours. Meanwhile, daily maximum temperatures of 35 to 40 °C are expected at Terkodi, Mender11, Quara, Lare, Fugnido, Abobo, Mankush and Metema.