Daily Weather Report November 09
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ በመካከለኛ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዲኦ፣ የሸካ፣ ከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ጉራጌ፣ አፍዴር፣ አኝዋክ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች፤ ደሬዳዋ እና ሐረር ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጪራ 49.8 እና በማሻ 60.0 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በወገል ጤና የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን 5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as West, East, Centeral, and South Western parts the country there was cloud coverage. Correspondingly, Light to Moderate rainfall recorded in Wolayita, Gamo, Gofa, Konso, South Omo, Gedeo, Sheka, Kefa, Bench Sheko, Dawuro, Gurage, Afder, Agnuak, East Gojam, North Shoa, South Gondar, West, Centeral, East, South, South East and South West Oromia zones; Dire Dawa and Harar. In Cira 49.8 and in Masha 60.0 MM heavy rainfall recorded. On the other hand, the daytime low temperatures in Wegel Tena 5°C recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ዶሎ፣ ዳዋ እና ፋፈን ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ ዞኖች፤ ደሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ እና ፋንቲ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የሌሊት እና የማለዳው ቅዝቃዜም ይቀንሳል፡፡
Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, North East, North West, Centeral, East, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Walayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Burji, Konso, South Omo, and Gedeo zones of South Ethiopia region: Sidama region zones; Sheka, Keffa, Konta, Bench Sheko, West Omo and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; Siti, Doolo, Dawa, and Fafen zones of Somali region; West, Centeral, East, South, South East, and South west zones of the Oromia region; Dire Dawa; Harari; Asosa, Metekal, Kamashi, and Mao Komo zones of Benishangul Gumuz region; Agnuak, Nuwer, Itang, and Majang zones of Gambella; West, North, South and Centeral Gondar, Awi zone,Waghemra, North and South Wollo, West and East Gojam, Oromo Ethnic special zone, and North Shoa Amhara region zones; West, North West, East, Centeral, South and South Eastern Tigray zones of region; Kilbiti and Fanti zones of Afar region. On the other hand night and morning temperatures will decrease in the highlands of the country.