Daily Weather Report November 08

Weather Summary for previous day

Nov. 7, 2026

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ በመካከለኛ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ጌዲኦ፣ ሸካ፣ አኝዋክ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በአምባ ማርያም 4.8 አና በወገል ጤና 5.0 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን 5ና ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Guyyaa kaleessa kutaaleen biyya keenya waqtiin bonaa yeroo rooba lammaffaa isaanii ta’an kibbaa fi kibba bahaa akkasumaas Lixa,Giddu galeessa fi Kibba Lixaa irratti uffisa duumessa qabu ture. kanaan walqabate:- Godinaalee Goofaa,Oomoo Kibbaa,Koonsoo,Geedi’oo,Shakkaa, Anyuwaak,Lixa,Kibba fi Kibba Lixaa Oromiyaatti irratti roobni salphaa hanga Giddu galeessa ta’e galmaa’ee jira. Karaa biraatiin: Ambaa Maariyaamitti 4.8 fi Wagaal Xeenaatti 5.0 ho’insii guyyaa gadi aanaan 5, fi 5°C gadi ta’e galmaa’ee jira.

Weather Forecast for next day

Nov. 9, 2026

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ኤረር፣ ጃራር እና ፋፈን ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ዞኖች፤ ደሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ሰሜን ምዕራብ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የሌሊት እና የማለዳው ቅዝቃዜም ይቀንሳል፡፡

Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, North West, East, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Walayita, Gamo, Gofa, Basketo, and Gedeo zones of South Ethiopia region: Sidama region zones; Sheka, Keffa, Bench Sheko, West Omo and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; West, East, South, and South west zones of the Oromia region; Dire Dawa; Harari; Asosa, Metekal, Kamashi, and Mao Komo zones of Benishangul Gumuz region; Agnuak, Nuwer, Itang, and Majang zones of Gambella. On the other hand, the northwest and central parts of the country will experience dry, sunny, and windy weather, while night and morning temperatures will decrease in the highlands of the country.