Daily Weather Report November 07
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ በመካከለኛ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በሸካ፣ ማጃንግ፣ ምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በአለም ከተማ 4.0 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as West, Centeral, and South Western parts the country there was cloud coverage. Correspondingly, Light to Moderate rainfall recorded in Sheka, Majang, West and South West Oromia zones. On the other hand, the daytime low temperatures in Ale Ketema 4.0 are recorded as below 5°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ሰሜን ምስራቅ፣ ሰሜን ምዕራብ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች እንደሚሆንና፤ ከዚሁም ጋር ተያይዞ የሌሊት እና የማለዳው ቅዝቃዜም በሰሜን ምስራቅ ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡
Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Walayita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo and Gedeo zones of South Ethiopia region: Sidama region zones; Sheka, Keffa, Bench Sheko, West Omo and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; West, East, South, and South west zones of the Oromia region; Agnuak, Itang, and Majang zones of Gambella. Meanwhile, the Northeastern, North Western, and Central parts of the country will experience dry, sunny, and windy weather conditions; in the country's highlands, daily minimum temperatures are expected to fall below 5 degrees Celsius, and the cold weather during the night and early morning time it will continue, over North Eastern.