Daily Weather Report November 06

Weather Summary for previous day

Nov. 5, 2026

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ፣ በመካከለኛ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በወገል ጤና 4.0፣ አምባ ማርያም 4.8፣ በአለም ከተማ 3.2፣ ጋሸና 4.4፣ ጊናጌር 2.9፣ ቡኢ 4.0፣ በሳጉሬ 5.0 እና በጅግጅጋ 5.0 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን 5°C ና ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as West, and south western parts the country there was cloud coverage. On the other hand, the daytime low temperatures in Wegel Tena 4.0, Amba Mariam 4.8, Alem Ketema 3.2, Gashena 4.4, Ginager 2.9, Bui 4.0, Sagure 5.0, and Jigjiga 5.0 are recorded as below 5°C.

Weather Forecast for next day

Nov. 7, 2026

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ ዞን፤ ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች እንደሚሆንና፤ ከዚሁም ጋር ተያይዞ የሌሊት እና የማለዳው ቅዝቃዜም ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡

Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Walayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Burji, Konso, South Omo and Gedeo zones of South Ethiopia region: All zones of the Sidama region; Sheka, Keffa, Bench Sheko, West Omo and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; Yem special Woreda, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones of Centeral Ethiopia region; South, and South west zones of the Oromia region; Agnuak, and Majang zones of Gambella. Meanwhile, South East Oromia, the northeastern, eastern, and central parts of the country will experience dry, sunny, and windy weather conditions; in the country's highlands, daily minimum temperatures are expected to fall below 5 degrees Celsius, and the cold weather during the night and early morning time it will continue, with increased strength.