Daily Weather Report November 03
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በ የአኝዋክ፣ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በወገል ጤና 2.5፣ በአለም ከተማ 3.4፣ መሀል ሜዳ 4.8፣ በሜሬሮ 4.5፣ በደብረ ብርሃን 0.8፣ በጅግጅጋ 4.0፣ በሐሮማያ 3.0 እና በእንዋሪ 4.0 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as West, and south western parts the country there was cloud coverage. Correspondingly, Light to Moderate rainfall recorded in Agnuak, South and South West Oromia zones. On the other hand, the daytime low temperatures in Wegel Tena 2.5, Alem Ketema 3.4, Mehal Meda 4.8, Meraro 4.5, Debre Berhan 0.8, Jigjiga 4.0, Haromaya 3.0 and Enewari 4.0 are recorded as below 5°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዶላ፣ ኮሬ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ቤንች ሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የአፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የማኦ ኮሞ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች እንደሚሆንና፤ ከዚሁም ጋር ተያይዞ የሌሊት እና የማለዳው ቅዝቃዜም ተጠናክሮ ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡
Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Walayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Burji, Konso, and Gedeo zones of South Ethiopia region: All zones of the Sidama region; Sheka, Keffa, Bench Sheko, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; Hadiya, Kembata, and Tembaro zones of Centeral Ethiopia region; South, South west, and Western zones of the Oromia region; Mao Komo zone of Benishangul-Gumuz region; Agnuak, Itang, and Majang zones of Gambella. Meanwhile, South East Oromia, the northeastern, eastern, and central parts of the country will experience dry, sunny, and windy weather conditions; in the country's highlands, daily minimum temperatures are expected to fall below 5 degrees Celsius, and the cold weather during the night and early morning time it will continue, with increased strength.