Daily Weather Report November 02

Weather Summary for previous day

Nov. 1, 2026

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በ የአዊ ዞን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደብረ ወርቅ 5.0፣ በአለም ከተማ 3.0፣ መሀል ሜዳ 2.6፣ አምባ ማርያም 4.0፣ ጉዶ በረት 5.0፣ በሳጉሬ 4.5፣ በሜሬሮ 4.5፣ በሁነቴ 3.2፣ በደብረ ብርሃን 1.0፣ በጅግጅጋ 3.0፣ በሐሮማያ 4.0 እና በአርሲ ሮቤ 5.0 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in the Bega second rainy season south and South East as well as West, and south western parts the country there was cloud coverage. Correspondingly, Light to Moderate rainfall recorded in Awi zone, West and South West Oromia zones. On the other hand, the daytime low temperatures in Debre Work 5.0, Alem Ketema 3.0, Mehal Meda 2.6, Amba Mariyam 4.0, Gudo Bert 5.0, Sagure 4.5, Meraro 4.5, Hunte 3.2, Debre Berhan 1.0, Jigjiga 3.0, and Arsi Robe 5.0 are recorded as below 5°C.

Weather Forecast for next day

Nov. 3, 2026

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዲኦ እና ባስኬቶ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች እንደሚሆንና፤ ከዚሁም ጋር ተያይዞ የሌሊት እና የማለዳው ቅዝቃዜም ተጠናክሮ ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡

Tomorrow will be cloudy over the Bega second rainy season south and South East as well as western, and south western parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Gedeo, and Basketo zones of South Ethiopia region: zones of the Sidama region; Sheka, Keffa, and Bench Sheko zones in the Southwest Ethiopia region; South west, and Western zones of the Oromia region; Asosa, and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Agnuak, Itang, and Majang zones of Gambella. Meanwhile, South East Oromia, the northeastern, eastern, and central parts of the country will experience dry, sunny, and windy weather conditions; in the country's highlands, daily minimum temperatures are expected to fall below 5 degrees Celsius, and the cold weather during the night and early morning time it will continue, with increased strength.