Daily Weather Report August 31

Weather Summary for previous day

Aug. 30, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ አውሲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ፣ ስልጤ እና ጉራጌ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በዳንግላ 45.7፣ በማሻ 133.0፣ በእዳጋ አርቢ 38.1 ፣በጋሳየ 32.5፣ በሸበል በረንታ 32.4፣ በጉንዶ መስቀል 31.4፣ በጊምቢ 82.4፣ በሊሙ ገነት 43.8 እና በጎንደር 30.3 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ መንደር11፣ ገዋኔ፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ መልካ ጀብዱ፣ መተሐራ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና በቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-43.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in Western, Northwest, North, Northeast, East, Southern, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Buno Bedelle, Horo Guduru, East and West Wollega, Southwest Shoa, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North Shoa, North and South Wallo, Northwest, East, South, Central and Southeast Tigray, Sheka, Bench Sheko, Assosa, Metekel, Awusi, Gabi, Hari, Silte, and Gurage zones light to moderate rainfall recorded. In particular, heavy rainfall was recorded in Dangila 45.7mm, in Masha133.0mm, in Edagaribi 38.1mm, in Gasay 32.5mm, in Shebel Berenta 32.4mm, in Gundo Meskel 31.4mm, in Gimbi 82.4mm, in Limu Genet 43.8mm, and in Gondar 30.3mm. On the other hand, in In Semera, Village11, Gewane, Fugnido, Gambella, Melka Jebdu, Metehara, Mehoni, Dire Dawa, Dallifage, Awash Arba, Gode and Kebre Dehar 35.0-43.4°C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Sept. 1, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ እና ባሌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ፋንቲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን፣ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ትግራይ፣ ሆሮ ጉዱሩ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue in similar way over the northern, western, northwestern, North East, South western, North East, and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem Wollega, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, and Bale, zones of the Oromia region; Addis Ababa: Dire Dawa; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North and South Wallo, Oromo Ethnic special zone, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones in Tigray region; Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Awusi, Fanti Gabi and Hari zones of Afar region; Siti zone of Somali region; All zones of the Sidama region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Halaba, Hadiya, Kambata and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Sheka, and Kaffa zones in the Southwest Ethiopia region; In addition West and South Gondar, North West and Centeral Tigray, Horo Guduru, and West Shoa zones heavy rainfall exceeding 30 mm is expected within 24 hours. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Gambella, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.