Daily Weather Report August 29

Weather Summary for previous day

Aug. 28, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በኮምቦልቻ 37.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሚኤሶ፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in Western, Northwest, Northeast, Southern, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem Wollega, North and East Shoa, West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North Shoa, North and South Wallo, and East Tigray zones light to moderate rainfall recorded. In particular, heavy rainfall was recorded in Combolcha 37.2mm. On the other hand, in In Meiso, Fugnido, Gambella, Metehara, Dire Dawa fi Gode 35.0-38.2°C the day time maximum temperatures recorded.

Weather Forecast for next day

Aug. 30, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ እና ባሌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ ዞን፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ እና ፋንቲ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማዕከላዊ ትግራይ፣ በደቡብ ጎንደር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ በገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue in similar way over the northern, western, northwestern, North East, South western, and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem Wollega, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, and Bale, zones of the Oromia region; Addis Ababa: West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North and South Wallo, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones in Tigray region; Agnuak zone of Gambella: Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Kilbati and Fanti zones of Afar region; All zones of the Sidama region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Halaba, Hadiya, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Sheka, and Kaffa zones in the Southwest Ethiopia region; In addition Central Tigray, South Gondar, Horo Guduru, East Wollega, and West Shoa zones heavy rainfall exceeding 30 mm is expected within 24 hours. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Gewane, Elidar, Fugnido, Gambella, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.