Daily Weather Report August 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አሶሳ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ ትግራይ እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጨዋቃ 35.2፣ በመተማ 36.8፣ በሾላ ገበያ 31.5 እና በማጀቴ 42.5 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ 37.0፣ ድሬዳዋ 35.0፣ መተሐራ 38.0 እና በጎዴ 36.2 በ°C የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in Western, Northwest, North, Northeast, East, Southern, Central, and Southwestern areas of our country, there was cloud coverage. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Addis Ababa; Dire Dawa: Jimma, Ilubabor, Horogudru, Buno Bedele, Kellem, the Eastern and western Wellega, West Hararghe, North, East, South-western and western Shoa, West Arsi, Asosa, Sheka, Bench Sheko, West Omo, Dawuro, West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North and South Wallo, North Shoa, East Tigray and Agnuak zone zones light to moderate rainfall recorded. In particular, heavy rainfall was recorded with amounts in Chewaka 35.2mm, in Metema 36.8mm, in Shola Gebeya 31.5, and in Majete 42.5 mm. On the other hand, in Fugnedo 37.0, Diredawa 35.0, Metehara 38.0, and Gode 36.2 in °C the maximum temperatures recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ፋንቲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሸካ፣ ካማሽ፣ ስልጤ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ሆሮ ጉዱሩ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue more intensify over the northern, western, northwestern, northeastern, eastern, southwestern, and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem Wollega, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji, Bale, West and East Hararghe zones of the Oromia region; Addis Ababa; Dire Dawa; Harari; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North and South Wallo, Oromo ethnic special zone, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones in Tigray region; Agnuwak, and Majang zones of the Gambella region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao-Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Awusi, Fanti, Gabi, and Hari zones of Afar region; Siti, and Fafan zones in the Somali region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; and Wolaita, Gamo, Gofa, and Gedeo zones in the South Ethiopia region. In addition, in South Gondar, Awi zone, West Gojam, Sheka, Kamashi, Silte, West Arsi, South West and West Shoa, Horo Guduru, and East Wollega zones heavy rainfall exceeding 30 mm is expected within 24 hours. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.