Daily Weather Report August 18

Weather Summary for previous day

Aug. 17, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና፣ አሶሳ፣ ሸካ፣ ዳውሮ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዴኦ፣ አኝዋክ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን እና ዋግኸምራ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በመተማ 61.7፣ በደባርቅ 35.2፣ በጊምቢ 77.3፣ በቢሾፍቱ 42.1፣ በቅዳሜ ገበያ 52.6፣ በጄምቤ 37.0፣ በሸበል በረንታ 37.1 እና በሀሮ 30.1 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ፉኝዶ፣ ጋምቤላ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ መሆኒ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-43.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in western, northwest, northeast, southern, central, and southwestern areas of our country, there was cloudiness. Correspondingly, Light to moderate rainfall accompanied in Addis Ababa; Jimma, Ilubabor, Horogudru, Buno Bedele, the eastern and western Wellega, East, South-western and western Shoa, Arsi, Bale and East Bale, Borena, Asosa, Sheka, Dawuro, Wolaita, Gamo, Gofa, Gedeo, Agnuak, western, North, South and Centeral Gondar, western and eastern Gojjam, Awi zone, and Waghemra zones light to moderate rainfall recorded. In particular, heavy rainfall was recorded with amounts in Metema 61.7mm, in Gimbi 77.3mm, in Bishoftu 42.1mm, in Kedame gebeya 52.6mm, in Jembe 37.0mm, Shebel Berenta 37.1 and in Haro 30.1 mm. On the other hand, in Semera, Fugnedo, Gambella, Dallifage, Awash Arba, Melka Jebdu, Diredawa, Metehara, Mehoni, and Kebridahar, the maximum temperatures reached 35.0–43.0°C.

Weather Forecast for next day

Aug. 19, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ፋንቲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue to intensify over the northern, western, northwestern, northeastern, eastern, southwestern, and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem Wollega, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Bale, West and East Hararghe zones of the Oromia region; Addis Ababa, Dire Dawa, and Harari; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North and South Wallo, Oromo ethnic special zone, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones in Tigray region; Agnuwak, Nuweer,Itaang and Majang zones of the Gambella region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao-Komo zones of Benishangul-Gumuz region; Awsi, Fanti, Kilbeti, Gabi, and Hari zones of Afar region; Siti, and Fafan zones in the Somali region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, West Omo, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; and Wolaita, Gamo, Gofa, and Gedeo zones in the South Ethiopia region. In addition, in Jimma, Buno Bedelle, Horo Guduru, East and West Wollega, Southwest and West Shoa, and South Gondar heavy rainfall exceeding 30 mm is expected within 24 hours. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.